መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን የሚመለከተው ረቂቅ ህግ መጽደቅ28 ታኅሣሥ 2001ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 28 2001የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለረጅም ጊዜ ሲያወዛግብና ሲያጨቃጭቅ የቆየውን መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ለመመዝገብና ለማስተዳደር የወጣውን ረቂቅ ህግ ዛሬ በአብላጫ ድምጽ አጸደቀው።https://p.dw.com/p/GT2Nከኤድስ ጋር የሚኖሩ ህጻናትን የሚረዳ የሚስዮናውያን ድርጅትምስል AP Photoማስታወቂያ ወኪላችን ታደሰ እንግዳው እንደዘገበው፡ ምክር ቤቱ ባለፈው ህዳር ሀያ ሶስት ቀን በረቂቅ አዋጁ ላይ ከመከረበት በኋላ ለዝርዝር እይታ ለህግና አስተዳደር፡ እንዲሁም፡ ለማህበራዊና ለውጭ መከላከያና ደህንነት ጉዳይዮች ቋሚ ኮሚቴዎች መርቶት ነበር። በምክር ቤት የተወከሉት የተቃዋሚ ፓርቲዎች እንደራሴዎች ረቂቁ ህግ አሁንም ጉድለት አለው በሚል አልደገፉትም።