1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መስቀል ክብረ በዓል- የዓለም የቅርስ

ቅዳሜ፣ ታኅሣሥ 5 2006
https://p.dw.com/p/1AZpu

ባለፈዉ ሰምወን አዘርባጃን መዲና ባኩ ላይ በተካሄደዉ ስምንተኛው የተባበሩት መንግስታት የሳይንስ የትምህርትና ባህል ማዕከል/UNESCO/ ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያዉ የመስቀል በዓል አከባበር በዓለም ቅርስነት ተመዝግቦአል። የኢትዮጵያ የመስቀል ባህላዊ ክብረ በዓል ኢትዮጵያ ቀደም ሲል ካስመዘገበቻቸው ዘጠኝ ታዳሽ ዓለም አቀፍ ቅርሶች በተጨማሪ አስረኛውና የመጀመሪያው የማይዳሰስና የማይጨበጥ (ኢንታንጀብል) ባህላዊ ቅርስ በመሆን ነዉ የተመዘገበዉ። በዕለቱ ዝግጅታችን የመስቀል ክብረ በዓል በዓለም አቀፉ የቅርስ መዝገብ እንዴት ሊመዘገብ እንደቻለ እና የዚህ ክብረ በዓል በዓለም መዝገብ መፃፉ ለኢትዮጵያ የሚያመጣዉን ፋይዳ ባለሞያዎችን አነጋግረን ዝርዝር ዘገባ ይዘናል።

አዜብ ታደሰ