መረጃ የማግኘት መብት
እሑድ፣ ኅዳር 26 2008ማስታወቂያ
መረጃን የመስጠት ኃላፊነት ላይ የተቀመጡ ተጠሪዎች ዘንድ ስለመረጃ ነፃነት አዋጁ ያለዉ ግንዛቤ ዉሱንነትም መረጃን የማግኘት መብቱ በአግባቡ ሥራ ላይ እንዳይዉል እንቅፋት መሆኑን የሚገልፁ አሉ። በሌላ በኩል መረጃን የማግኘት መብትን የሚደነግገዉ አዋጅ በራሱ መረጃን መከልከልን የሚያበረታታ ነዉ በማለት ሕጉ ራሱ እንዲመረመር የሚጠይቁም አሉ። መረጃ የማግኘት መብት በዓለም አቀፍ ደረጃ ስለተደነገገና ተቀባይነት ስላገኘ ብቻ ሳይሆን ከሰብዓዊ መብቶች አንዱ እንደመሆኑ ተግባራዊነቱ እንዴት ሊቀጥል ይችላል? ሊደረጉ የሚገባቸዉ መሻሻሎችስ? ዶቼ ቬለ በዚህ ላይ ዉይይት አካሂዷል። ዉይይቱን ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ።
ሸዋዬ ለገሠ
ልደት አበበ