መሃይምነት ድራማ ክፍል 4 -ትምህርትን ማጠናቀቅ
ረቡዕ፣ መጋቢት 4 2005ማስታወቂያ
በተፈጥሮዋ ነፃ የሆነችውና በአገር አስጎብኚ ድርጅት የምትሰራዋ ዙሪያሽ በጓደኛዋ ልእልት የትምህርት ጉዳይ በእጅ አዙር አማካሪዋ መሆኗን የልእልት ቤተሰቦች ጠርጥረዋል፡፡ በመሆኑም የልእልት እናት ወ/ሮ መብራት ዙሪያሽን እየጠሏት በመሄዳቸው ልክልኳን የሚነግሩበት አጋጣሚ እየጠበቁ ነው፡፡ ዛሬ ጧት ዙሪያሽ ሁለት አውሮፓውያን አገር ጎብኚዎች ማለትም የ67 አመቱ ጡረተኛ አዛውንት አቶ Handrik እና የ62 አመቷ ባለቤታቸው ወ/ሮ Susanna ወደ ልእልት አባት የብረታ ብረት ድርጅት ይዛ ትመጣለች ብሎ የጠበቀ የለም፡፡ ምን ያጋጥም ይሁን? ክፍል 4 ጭውውቱን ተከታተሉ፡፡