መሃይምነት ድራማ ክፍል- 1 የተረገመች ቀን
ሰኞ፣ ሚያዝያ 7 2005ማስታወቂያ
የሃምሳ ሁለት አመት አዛውንቱ አቶ ወልዳይ የሶስት ልጆች አባት ሲሆኑ በአንድ ትንሽ ከተማ የብረታ ብረት ስራ ድርጅት ባለቤትና አስተዳዳሪ ናቸው፡፡ አቶ ወልዳይ አልተማሩም፡፡ በመሆኑም አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን የመረዳት ብቃት ካላቸው ወጣቶች ጋ መፎካከር እየከበዳቸው ነው፡፡ ለተወሰኑ ጊዜያት በትእዛዝ የሚሰሩ ነገሮች ጠፍቷል፡፡ ተሰርተው በሽያጭ የተዘጋጁትም ቢሆን ገዢ የለም፡፡ አቶ ወልዳይ ከቀን ወደቀን እየደኽየ የመጣውን ቤተሰባቸውን ገሸሽ ማድረግ ጀምሯል፡፡ የመጀመሪያውን ክፍል ይከታተሉ።