1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሕገወጥ አዘዋዋሪዎችና የአውሮጳ ኅብረት ዕቅድ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 4 2007

ከተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች በተለይም ከአፍሪቃ በሊቢያ በኩል የሜድትራኒያን ባሕር አቋርጠዉ ወደ አውሮጳ የሚጓዙ ስደተኞች ቁጥር እየተበራከተ ነው። በዛው መጠን ባሕር ውስጥ ሠጥመው የሚያልቁት ስደተኞችም በርካቶች ናቸው። እጅግ አደገኛውን የባሕር ላይ ጉዞ የሚያደራጁት ሕገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ናቸው።

https://p.dw.com/p/1FOa1
Italien Flüchtlinge in Lampedusa
ምስል Reuters/A. Bianchi

ባለፈዉ ወር የሜድትራኒያንን ባሕር ለማቋረጥ ሲሞክሩ ከ800 በላይ ስደተኞች ካለቁ ወዲሕ የአውሮጳ ኅብረት ስደተኞቹን በሚያሸጋግሩ ነጋዴዎች ላይ የኃይል ርምጃ ለመውሰድ የሚያስችለውን ዕቅድ ነድፏል።ዕቅዱን ገቢር ለማድረግ ሕጋዊ ተቀባይነት እንዲኖረው የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ጥበቃ ምክር ቤትን ጠይቋል። ዕቅዱ ተግባራዊ ከሆነ የአውሮጳ ኅብረት በሜዲትራኒያን ባሕር ላይ የተሰማሩ ሕገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ላይ ወታደራዊ ጥቃት መሰንዘር ያስችለዋል። ስደተኞችን ለአውሮጳ አባል ሃገራት በኮታ መልክ ማደላደልን በተመለከተ ለመምከር የሕብረቱ አባል ሃገራት የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚንሥትሮች ነገ ብራስልስ ውስጥ እንደሚሰባሰቡ ተገልጧል። የብራስልሱ ወኪላችን ገበያው ንጉሤ የሚከተለውን ዘገባ ልኮልናል።

ገበያው ንጉሤ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ