ሕይወት እምሻው በፌስቡክ
ዓርብ፣ ጥር 29 2007ማስታወቂያ
አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኝ አንድ - ኤም ኤስ ኤች በሚባል መንግሥታዊ ባልሆነ ድርጅት ውስጥ የጤና ዘመቻ አስተባባሪ ሆና የምታገለግለው ሕይወት፤ ትርፍ ጊዜዋን የምታሳልፈው ድርሰቶችን፣አጫጭር ታሪኮችን በመፃፍ ነው።
የ 33 ዓመቷ ጎልማሳ - ሕይወት የፁሁፍ መንፈሱን ያገኘሁት ከአባቴ ነው ትላለች። ፌስ ቡክ ላይ ብዙ አንባቢዎች አሏት። « ነቆራ እና ሌሎችም ወጎች ከሕይወት እምሻው ጋር» ይላል የሕይወት እምሻው የፌስ ቡክ ገፅ፤ ከ 71 600 በላይ ሰዎች ገጿን ወደውላታል። በርካቶችም ከታሪኩ በታች አስተያየታቸውን ይገልፃሉ። ነገር ግን ሕይወት አንባቢዎቿን እጅጉን ያስደሰታቸው ታሪክ ይህ ነው ለማለት ያስቸግራል ትላለች።
ሕይወት እስካሁን የፃፈቻቸውን ታሪኮች በቁጥር አታውቃቸውም። ነገር ግን ረዝም የሚሉት እስከ 500 ይደርሳሉ ትላለች።
ሕይወት እምሻው እና በትርፍ ሰዓቷ የምትፅፋቸው አጫጭር ታሪኮች ጥቂቱን ከዚህ በታች በድምፅ ያገኙታል።
ልደት አበበ
አርያም ተክሌ