1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሐረር ከተማና መስህቦችዋ

ሐሙስ፣ ጥር 15 2006

በኢትዮጵያ ጅብ ተከብሮ ስጋ ጎርሶ፤ ገንፎ ተገንፍቶ ቀርቦለት የሚኖረዉ ሐረር ከተማ ላይ ነዉ። ከጥር ስምንት እስከ 10 የሐረሬ ጅቦችና የከተማዋ ነዋሪዎች አንድ ላይ የሚያከብሩት የአሹራ በዓል ይሰኛል። ሐረሪዎች የሚያከብሩት ሶስት በዓላቶች መካከል ለጅብ ገንፎ የማብላት ስነ-ስርዐት አንዱ ነዉ።

https://p.dw.com/p/1AwGp
Stadtmauer von Harar Stadt im Südosten von Äthiopien
ምስል Azeb Tadesse Hahn

በምስራቅ ኢትዮጵያ ከአዲስ አበባ 525 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘዉ ሐረር ከተማ አምስት በሮች ባሉትና ጀጎል ተብሎ በሚጠራዉ ዝነኛ ግንብ የተከበበች ስትሆን፤ በሰባተኛዉ እና ዘጠነኛዉ ክፍለ ዘመን መቆርቆርዋን፤ በከተማዋ የሚገኙ ታሪክ አዋቂዎች ይናገራሉ። የዕለቱ የባህል ቅንብራችን የሐረር ከተማን ያስቃኘናል። ከምስራቅ አፍሪቃ ጥንታዊ ከተሞች አንዷ በመሆን በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት UNESCO በቅርስነት የተመዘገበችዉ ሐረር ከተማ 4ኛዉ የስልምና ሃይማኖት ቅዱስ ከተማ ተብላም ትጠራለች። የሐረሪ ህዝብ ክልላዊ መንግሥት የባህል ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ተጠሪ አቶ አዩብ አብዱላሂ ስለ ሐረር ከተማ ጥንታዊነት እንዲህ ያስረዳሉ። የጀጎል ግንብ ማለት ሐረሪ ዎች መኖርያ ማለት ነዉ ሲሉም ገልፀዉልናል።

Innenausstattung Harar Äthiopien
ምስል Azeb Tadesse Hahn

አባድር ጦም አያስድር የሚባልላት የሀረር እና የሐረር እንብር ት፤ በርካታ እሴቶች እናዳልዋት፤ ህዝቡሟም ተቻችሎ መኖሩን የሐረሬ ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ተጠሪ አቶ አዩብ ይናገራሉ።

ለቱሪስት መስብዕነት ሀረሪ ላይ ጅብ ባለዉለታ ነዉ የሚሉት አቶ አዩብ ከተማዋን ጅብ ስጋ ማብላት የተጀመረዉ የጀጎል ግንብ ሲገነባ ለከተማዋ ንፅህና ሲባል ከየቤቱ የሚወጣዉን የምግብ ትርፍራፊ እና ቆሻሻ እንዲለቃቅም ሲባል ነዉ ሲሉ አጫዉተዉናል በግንቡ ዙርያ ለጅብ መግብያ የተሸነቆረዉ ቀዳዳ ወረባ ኑድል መባሉንም ነግረዉናል። ጅብን በማብላት ስራ ከተሰማራ ወደ 22 ዓመታት እንደሆነዉ አቶ ሙልጌታ ወልደማራያም የስጋ ማከፋፈያ ቄራ ዉስጥ በመላላክ ይሰራ እንደነበረ ይገልጻል.

በሀገራችን በኢትዮጵያ ጅብ ተከብሮ ስጋ ጎርሶ፤ ገንፎ ተገንፍቶ ቀርቦለት የሚኖረዉ ሐረር ከተማ ላይ ነዉ። ከጥር ስምንት እስከ 10 የሐረሬ ጅቦችና የከተማዋ ነዋሪዎች አንድ ላይ የሚያከብሩት የአሹራ በዓል ይሰኛል። ሐረሪዎች ይላሉ የከተማዋ ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ተጠሪ አቶ አዩብ አብዱላሂ ሐረሪ ዎች የሚያከብሩት ሶስት በዓላቶች አሉዋቸዉ ከዝያም መካከል ለጅብ ገንፎ የማብላት ስነ-ስርዐት አንዱ ነዉ።

Hyänen füttern in Harar ist einen Touristen Attraktion ACHTUNG SCHLECHTE QUALITÄT
ምስል Azeb Tadesse Hahn

የሐረሪ ህዝብ ክልላዊ መንግሥት የባህል ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ ዋና ተጠሪ አቶ ሙህየዲን አህመድ እንደሚሉት በግማሽ ዓመት ዉስጥ ከተማዋን ከ 7000 በላይ የዉጭ ዜጋ ይጎበኛታል።

ስለ ሐረር ታሪካዊ እሴቶችና ምስብዖችዋ በጥቂቱ የቃኘንበት ለዕለቱ ዝግጅታችን መሳካት ቃለ ምልልስ የሰጡንን በዶቼ ቬለ ጣብያ ስም አመሰግናለሁ አድማጮች በባህል መድረክ ላይ ያላችሁን አስተያየት ላኩልን። ሙሉዉን ቅንብር የድምፅ ማድመጫዉን በመጫን ያድምጡ!

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሀመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ