1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሊቃነ-ጳጳሳት-85 አመት ሆናቸዉ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 11 2004

በያዝነዉ ሳምንት መጀመርያ የሮማ ካቶሊካዊ ቤተክርስትያን ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክት 16ኛ 85 አመት ሆናቸዉ። ቤኔዲክት 16ኛ በርካታ ህዝብ ተሰብስቦ ይህን ያህል ምኞት ሲቸራቸዉ ለሳቸዉ የመጀመርያ ነበር። በዚህ እለት ወደ 200 የሚጠጉ እንግዶች የሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክት 16ኛ 85 ኛ የልደት በአል ለማክበር ነበር የተሰበሰቡት።

https://p.dw.com/p/14hF1
ምስል AP

በያዝነዉ ሳምንት መጀመርያ የሮማ ካቶሊካዊ ቤተክርስትያን ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክት 16ኛ 85 አመት ሆናቸዉ። ቤኔዲክት 16ኛ በርካታ ህዝብ ተሰብስቦ ይህን ያህል ምኞት ሲቸራቸዉ ለሳቸዉ የመጀመርያ ነበር። በዚህ እለት ወደ 200 የሚጠጉ እንግዶች የሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክት 16ኛ 85 ኛ የልደት በአል ለማክበር ነበር የተሰበሰቡት። በዚህ ዝግጅት ላይ የባየር ግዛት ጠቅላይ ሚስቴር ሆርስት ዜ ሆፈርም ተገኝተዉ ነበር። በልደት ክብረ በአል ላይ የተገኙት እንግዶች ዮሴፍ ራትዚንገር በባየር ግዛት ሳሉ የሚያቁዋቸዉ እና አሁን የሮማ ካቶሊካዊ ቤተክርስትያን ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክት 16ኛ ከሆኑ በኋላ የሚያዉቋቸዉ የቅርብ ሰዎች ናቸዉ።

«እንኳን ደስ አልዎ ቅዱስ አባታችን» የባየር ግዛት ጠቅላይ ሚስቴር ሆርስት ዜ ሆፈር ለሊቃነ-ጳጳሳት ቤኔዲክት 16ኛ ያቀረቡት የደስታ መግለጫ ነበር። ቤኔዲክት 16ኛ በመልሳቸዉ «በዚህ ሰአት ምን መመለስ እንዳለብኝ ለመልስ የሚሆን በቂ ቃላትም ማግኘቴን አላዉቅም። የባየርን ህዝብ የልብ ሃሳብ ነዉ እርሶ በቃላት የገለጹት»

ለእንኳን አደረስዎ መግለጫዉ ያቀረቡት የምስጋና ቃል ነበር ።

Vatikan Papst Benedikt XVI hat Geburtstag Horst Seehofer
የባየር ግዛት ጠቅላይ ሚስቴር ሆርስት ዜ ሆፈር ለሊቃነ-ጳጳሳት ቤኔዲክት 16ኛምስል dapd

«ሰላም የእግዚአብሄር በረከት እና ጤንነት ይስጦ» የሮማ ካቶሊካዊ ቤተክርስትያን ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክት 16ኛ ወንድም ጂዎርጅ ራትዚንገር ወንድማቸዉ ቤኔዲክት አስራ ስድስተኛ የ85ኛ አመት የትዉለድ ቀናቸዉ እለት ያስተላለፉት የእንኳን አደረሰዎ ምኞት መግለጫ ነበር። የ 85 አመቱ ቤኔዲክት 16ኛ ልደታቸዉን ሲያከብሩ በርግጥ ጤንነታቸዉ ሁኔታ እጅግም መሆኑ ነዉ የሚነገረዉ። ይንኑ ቀን በማስመልከት ከአለም አገራት የተዉጣጡ ምዕመናንም ሮማዋን ቫቲካን ለመጎብኘት እየጎረፉ ነዉ። እንደ ቤኔዲክት 16 ኛ ቃል አቀባይ ፊድሪኮ ላምባርዲ ግን ሊቃነ-ጳጳሳት ቤኔዲክት 16ኛ ቫቲካን በምዕመናን ብትሞላም ለሊቃነ-ጳጳሳቱ ምንም ችግር የለባቸዉም፥ ጤንነታቸዉ በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛል፣ አልደከማቸዉም ሲሉ ገልጸዋል። በትዉልድ ስማቸዉ ዮሱፍ አሎስዮስ ራትዚንገር በመባል ይታወቁ የነበሩት ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክት 16ኛ በጎርጎረሳዉያኑ 1927 ሚያዝያ 8 በደቡባዊ ጀርመን በባየር ግዛት ተወለዱ። የዝያንግዜዉ ዮሱፍ አሎስዮስ ራትዚንገር የካቶሊክ እምነትን እጅግ በሚያጠብቁ ቤተሰብ ዉስጥ ነዉ በካቶሊክ ሃይማኖት ታንጸዉ ያደጉት። ዮሴፍ እቅስና ማዕረግን ከተቀበሉ እና የከፍተኛ ትምህርታቸዉን በሃይማኖት ትምህርት ካጠናቀቁ በኋላ፣ በቦን፣ ሙንስተር፣ ቱቢንገን እና ሪግንስበርግ በተሰኙ የጀርመን ከተሞች በሚገኙ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በፕሮፊሰርነት ማዕረግ የሃይማኖት ትምህርትን ሰጥተዋል። ቤኔዲክት በትምህርት ቤት የሃይማኖት ትምህርት ሲሰጡ ሳለ ብዙ ሳይቆዩ፣ የቤተክርስትያን ስልጣን ተዋርድን ያገኛሉ። ይኸዉም እንደ ጎርጎረሳዉያኑ 1977 ዓ,ም በደቡብ ጀርመን የሙኒክ እና የፍራይዚንግ ከተማ ሊቃነ-ጳጳስ ሆነዉ ይሾማሉ። ብዙም ሳይቆይ እ,ጎ,አ 1981 ዓ,ም የቀድሞዉ የሮማ ካቶሊካዊ ቤተክርስትያን ሊቃነ ጳጳሳት ዮሃንስ ፓዉል ሁለተኛ ደብዳቤ በመላክ በቫቲካን ትልቅ ሃላፊነት ቦታ እንዲቀመጡ ስራ ሰጥዋቸዉ።

85. Geburtstag von Papst Benedikt. XVI
ምስል AP

የሮማ ካቶሊካዊ ቤተክርስትያን ሊቃነ-ጳጳሳት ዮሃንስ ፓዉል ሁለተኛ ከዚህ አለም ከተለዩ በኋላ በቫቲካን ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ሊቃነ-ጳጳሳትን ለመሾም በተደረገዉ ፈጣን የተባለለት ምርጫ ጀርመናዊዉ ዮሴፋ ራትዚንገር ይመረጣሉ። በዝያን ግዜ የተሰጣቸዉም የማዕረግ እርከን የሽግግር ሊቃነ-ጳጳሳት እንዲሆኑ ነበር። ግን ከዝያ ግዜ ጀምሮ የሮማ ካቶሊካዊ ቤተክርስትያን ሊቃነ- ጳጳሳት ቤኔዲክት 16ኛ በመሆን፣ ሰባተኛ አመታቸዉን እንሆ ዘንድሮ ይዘዋል። ቤኔዲክት 16ኛ በያዙት መንበር በርካታ ራዕይን ይዘዉ ነዉ ጉዞን የጀመሩት። በክርስትና ሃይማኖትን እንዲሁም በአለም ስላለዉ ሃይማኖት ዉይይት እንዲደረግ ጥረት አድርገዋል። ማርቲን ሉተር የሃይማኖት ታህድሶ ካደረገባት ከጀርመን የመጡት የሮማ ካቶሊካዊ ቤተክርስትያን ሊቃነ-ጳጳሳት ቤኔዲክት 16ኛ በጀርመን ቀዝቅዞ የሚታየዉን የክርስትና እምነት ለማጎልበት ጥረት አድርገዋል። እንብዛም ስኬትን ባያገኙም። በሌላ በኩል ግ ቤኔዲክት በምስራቅ ከሚገኙ አብያተ ክርስትያን ባደረጉት ዉይይት ዉጤትን አግኝተዋል። በጎርጎረሳዉያኑ 2006 ዓም ቤኔዲክት 16ኛ ከካቶሊክ እና ከኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስትያናት ጋር ዉይይትን አድርገዉ ቱርክ ኢስታንቡል ላይ ቅዱስ ፓትርያርክ ባርቶሎሚኦስን እግኝተዋቸዋል። ይህም ግንኙነታቸዉ ታሪካዊ መሆኑ ተነግሮአል።

ትዉልደ ጀርመናዊዉ የሮማ ካቶሊካዊ ቤተክርስትያን ሊቃነ- ጳጳሳት ቤኔዲክት 16ኛ በአለም ዙርያ የሚያገኙት ከፍተኛ አድናቆት በአንዳንድ ጉዳዮች ሁኔታዉ ዳመና ሳያጠላበትም ተስተዉሎአል። ለምሳሌ በካቶሊካዊት ቤተ-ክርስትያን ዙርያ እንደ ጎርጎረሳዉያን አቆጣጠር በ2010 ዓ,ም በጀርመን፣ በአየርላንድ እና በዩኤስ አሜሪካ ህጻናት ላይ ወሲባዊ ጥቃት መፈጸሙ መጋለጡ አንዱ በካቶሊካዊ ቤተ-ክርስትያን ዉስጥ የተፈጸመ እጅግ ከባዱ ወንጀል ነበር። በዚህ ምክንያት በጉብኝት በተገኙባቸዉ አገሮች ሁሉ ከባድ ነቀፊታ ሲጣልባቸዉም ተስተዉሎአል። ለምሳሌ በጎርጎረሳዉያኑ 2008 ዓም ዮናይትድ ስቴትስን በጎበኙበት ወቅት የወሲብ ጥቃት የደረሰባቸዉ ነቀፊታቸዉን በማሰማት አደባባይ ወተዋል።

Vatikan Papst Benedikt XVI hat Geburtstag
ምስል dapd

በሌላ በኩል ሊቃነ- ጳጳሳት ቤኔዲክት 16ኛ በአለም ዙርያ በሚገኙ አገሮች ጉብኝት ሲያደርጉ በሃይማኖት ረገድ ብቻ ሳይሆን በፖለቲካም አኳያ ጥሩ ስራን መስራታቸዉ ይታወቃል። የቀድሞ ዮሱፍ አሎስዮስ ራትዚንገር የሊቃነ-ጳጳሳት ቦታዉን ከያዙ በኅላ በመጀመርያ የትዉልድ አገራቸዉን ጀርመንን ነበር የጎበኙት። እጎአ 2005 አም የአለም የወጣቶች ቀን በጀርመን ኮለኝ ከተማ ሲከበር ከአለም የተሰባሰቡ ወጣቶች እንደ አንድ ታዋቂ የአለም ኮከብ ነበር አቀባበል የተደረገላቸዉ። የሊቃነ- ጳጳሳት ነቃፊ እንድሆኑ የሚታወቁት ብሪታንያዉያን እንኳ ቤኔዲክት 16ኛ በአገሪቷ ጉብኝት ባደረጉ ግዜ ሙሉ ደስታ የታየበት ከፍተኛ አቀባበል ነዉ የተደረገላቸዉ። በቅርቡ ላቲን አሜሪካን በጎበኙበት ወቅት የነዋሪዉን ልብ በደስታ መሙላታቸዉም ተነግሮላቸዋል። በተለይ በኩባ ፊደል ካስትሮና ወንድማቸዉ ራዉል ካስትሮ በቤኔዲክት ጉብኝት እጅግ መደሰታቸዉ ተገልጾአል። በዚህም እስከ ዛሪ በሶሻሊስትዋ ኩባ የትንሳኤ በአል መዳረሻ የስቅለት ቀን ዝግ ያለነበረዉ የመንግስት መስሪያ ቤት ከሚቀጥለዉ አመት ጀምሮ በበአልነት እንዲመዘገብና የእረፍት የበአል እንዲሆን ከሶሻሊስት አራማጆቹ ተደንግጎአል።

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሃመድ