1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሉፍታንዛ ወደ አስመራ በረራ ማቆሙ

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 26 2006

የጀርመን አየር መንገድ የሆነው ሉፍታንዛ ከፍራንክፈርት ከተማ ወደ አስመራ ኤርትራ በረራ ካቋረጠ ሳምንት አንዳለፈው አስታወቀ።

https://p.dw.com/p/1ABpj
ARCHIV - Die Trachten-Crew der Lufthansa posiert am 21.09.2012 in München (Bayern) am Flughafen vor ihrer Maschine vor dem Flug LH412 nach New York. Bei der Lufthansa sind erneute Streiks der Flugbegleiter vom Tisch. Im monatelangen Tarifkonflikt gab es eine Einigung. Foto: Felix Hörhager dpa +++(c) dpa - Bildfunk+++
ምስል picture-alliance/dpa

የጀርመን አየር መንገድ የሆነው ሉፍታንዛ እስከ ጥቅምት 17, 2006 ዓ ም ድረስ ከፍራንክፈርት-አስመራ በሳምንት ሶስት ቀን ይበር ነበር። ይሁንና በጀርመን እና በኤርትራ መንግስት መካከል መሟላት የነበረባቸው የአየር ትራንስፖርት ደንቦች ባለመቅረባቸው፤ ለጊዜው ወደ አስመራ በረራውን ማቋረጡን ሉፍታንዛ ይፋ አድርጓል። ሆኖም አየር መንገዱ ሁለቱ አገሮች ስምምነት ላይ ሊደርሱ ያልቻሉበትን ምክንያት አልገለጸም።

በጥቅሉ « የአየር ትራንስፖርት ደንቦች ባለመሟላታቸው ስምምነቱ አልተራዘመም፤ በዚህም የተነሳ በረራው ሊቋረጥ ችሏል» ያሉት ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉት የሉፍታንዛ የሕዝብ ግንኙነት ባልደረባ፤ አክለውም ይህን አስመልክቶ በሁለቱ ሀገራት ስለሚደረገው ድርድር የበለጠ መረጃ እንደሌላቸው ተናግረዋል።

Beschreibung: Beladung von Lufthansa Cargo Maschinen Foto: FRA F/CI, Lufthansa Cargo Frei zur Verwendung für Pressezwecke
ምስል FRA F/CI, Lufthansa Cargo

«እኛ እንደ አንድ የአየር መንገድ ወደ ሌላ ሀገር እንድናበር የሚፈቀድልን የተወሰነ የበረራ ብዛት አለ።» ይህ የስምምነቱ አካል ነውም ብለዋል። ከዚህም ሌላ ከመጨው ታህሳስ ወር ጀምሮ ወደ ጋቦን እና ዴሞክራቲክ ሪፖብሊክ ኮንኮ ሉፍታንዛ በረራውን ሙሉ በሙሉ እንደሚያቆም ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል። ወደእነዚህ ሃገራት የሚደረጉ በረራዎች መቆም ምክንያት የሉፍታንዛ አየር መንገድ ትርፋማ አለመሆን እንደሆነም ዘገባው ያስረዳል። ይሁንና ሉፍታንዛ ወደ አስመራ -ኤርትራ በረራውን ያቋረጠበት ምክንያት ትርፋማ ካለመሆን ጋ ፍፁም እንደማይገናኝ ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል።

በትክክል የሚታወቀው ግን በረራው ለጊዜው እስከ ህዳር 15, 2006 ዓ ም ድረስ መቋረጡን ነው። ከፍራንክፈርት ተነስቶ ወደ አስመራ የሚበር ብቸኛ አየር መንገድ እንደሆነ የገለፀው ሉፍታንዛ፤ በረራው በመቋረጡ የተነሳ፤ አዲስ ተሳፋሪዎችን እንደማይቀበል ቃል አቀባዩ ዛሬ ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል። በረራው የማቋረጡ ርምጃ ከመወሰዱ አስቀድሞ ቲኬት የገዙ ተሳፋሪዎችን በተመለከተ ደግሞ ሲያስረዱ ከሉፍታንዛ ጋ በትብብር ከሚሠራው የግብፅ አየር መንገድ- ማለት «ኢጂብት ኤር» ጋር በመስማማት ሉፍታንዛ መንገደኞቹን በካይሮ በኩል አሳፍሮ እንደሚልክ ዘርዝረዋል።

እስከ ኅዳር 15 ሉፍታንዛ ምን ለውጥ ይጠብቃል ለሚለው ጥያቄ፤ «አስፈላጊ የሆኑት ደንቦች ተሟልተው በሳምንት ሶስት ጊዜ በረራችንን ወደ አስመራ እንቀጥላለን ብለን ተስፋ እናደርጋለን» የሚል ነዉ የአየር መንገዱ የሕዝብ ግንኙነት መልስ።

ልደት አበበ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ