በርካቶችም የተወለዱበትና ያደጉበትን ቀዬ እንዲለቁ አስገድዷል። እያሰለሰ ለሚታየዉ ረሃብና ድርቅ ዛሬም አገሪቱ መፍትሄ ማበጀት የቻለች አትመስልም። በሎንዶን ለእይታ የቀረበዉ አንድ ጥናታዊ ፊልም ይህንኑ ሃቅ ያመላክታል። በአንድ ወጣት አርሶ አደር ህይወት ዙሪያ ተመስርቶ እዉነታዉን የፈተሸዉን ጥናታዊ ፊልም በብሪታንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አብዛኛዉን አርሶ አደር አይወክልም ሲል ተችቷል።
ሃና ደምሴ/ሸዋዬ ለገሠ