ለፋሽስት ጣሊያን ወረራ ግፍ ካሳ መጠየቁ
ሰኞ፣ መስከረም 17 2008ማስታወቂያ
ዓለም አቀፍ ሕብረት ለፍትሕ - የኢትዮጵያ ጉዳይ ድርጅት ባካሄደዉ በዚህ ጉባኤ በወረራዉ ወቅት ስለተፈፀመዉ ግፍ እና ቫቲካንን ድጋፍ የዘረዘሩ የጥናት ጽሑፎች መቅረባቸዉን በቦታዉ የተገኘዉ የዋሽንግተኑ ወኪላችን መክብብ ሸዋ በላከዉ ዘገባ ገልጾልናል። በፋሺስት ኢጣልያ ወረራ ወቅት ኢትዮጵያ ላይ የተፈፀመዉ አሰቃቂ የጦር ወንጀል ይቅርታ እንዲጠየቅ ከሃገሪቱ የተዘረፈዉ ንብረት እንዲመለስ በሚል ፍትህን የሚጠይቁ ጽሑፎች በምሑራን አንደበት ተተንትነዋል።
መክብብ ሸዋ
አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሰ