ለደን ጥበቃ የኅብረተሰብ ተሳትፎ
ማክሰኞ፣ ጥር 7 2005ማስታወቂያ
በሀገሪቱ የተሻለ የደን ሃብት ይገኝባቸዋል የሚባሉ አካባቢዎች ሁኔታም ከወን ወደቀን ለጉዳት መዳረጋቸዉ ቢገለፅም ኅብረተሰቡን በማሳተፍ ዉጤት ለማምጣት ጥረት ተጀምሯል።
አቶ ሉሉ ሊካሳ በፋርም አፍሪካና SOS ሳህል ፕሮጀክት የባሌ ፕሮግራም አስተባባሪ ናቸዉ። ለረዥም ዓመታት ጠባቂዎች እየተቀጠሩ ይከታተሉት የነበረዉ የደን ሃብት ከጭፍጨፋ ባለመዳኑ አዲስ ስልት ማለትም አሳታፊ የደን አስተዳደር መርሃግብር ተግባራዊ ለማድረግ መታቀዱን ነዉ የገለፁልን።
የደን ሃብትን መጠበቅ ለአካባቢዉ ኗሪዎች ከሚሰጠዉ የዕለት ከዕለት ጥቅም ባሻገር የአየር ንብረት ሚዛንን በመጠበቅ ደኑ ዉስጥ የሚገኘዉን ብዝሃ ህይወት እንደሚታደግ ይታመናል። የደን ሃብት ጥበቃ በአንድ ተቋም ወይም መንግስታዊ መስሪያ ቤት ብቻ የሚከናወን ከሆነ የተፈለገዉን ዉጤት ማምጣት እንደማያስችል ከታየበት ተሞክሮ በመነሳት ላለፉት ዓመታት ኅብረተሰቡን ያሳተፈ የደን አስተዳደር ሥራ ላይ ዉሏል።
ሸዋዬ ለገሠ
አርያም ተክሌ