ለደቡብ ሱዳን ወሳኝ የተባለ የሰላም ስምምነት መፈረሙ
ማክሰኞ፣ ጥቅምት 23 2008ማስታወቂያ
በኢጋድ፣ በአፍሪቃ ህብረት እና በአጋር ድርጅቶች ሸምጋይነት በተደረሰው ስምምነት መሰረት፣ ስልጣን ላይ የሚገኘዉ የደቡብ ሱዳን ሕዝቦች ነፃ አዉጭ ንቅናቄ SPLM፤ በዚሁ ስም የሚጠሩ ተቀናቃኞቹ SPLM (IO) ወይም ወይም ኢን ኦፖዚሽን» እንዲሁም SPLM (A) የሚባሉት ቡድኖች ደቡብ ሱዳን ዉስጥ ጦርነት ለማቆም ተስማምተዋል። የደቡብ ሱዳን የፖለቲካ ቡድኖች፣ ኃይሎቻቸውን በማራራቅ በተለያዩ ካምፖች ለማሰባሰብ፣ እንዲሁም፣ የጁባ እና የሌሎች ከተሞችን ከጦር እንቅስቃሴ ነፃ ለማድረግ እና የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት የሚያስችላቸዉን መንገድ ለማስተካከል ነው የተስማሙት።
ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
አርያም ተክሌ
ሸዋዬ ለገሠ