1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለኢትዮጵያ የታጩት አዲሱ የአሜሪካ አምባሳደር 

ሐሙስ፣ ሐምሌ 6 2009

በኦባማ ዘመነ ስልጣን በተለያዩ የአፍሪቃ ሃገራት ተሾመዉ የነበሩትን አምባሳደር ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለኢትዮጵያ በእጩ አምባሳደርነት አቀረቡ ። የአምባሳደሩ ስልጣን በሴኔቱ የዉጭ ጉዳይ ኮሚቴ ይሁንታን ካገኘ በኋላ ተመራጩ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚሄዱ ታዉቋል።

https://p.dw.com/p/2gUVe
USA Amok Flagge
ምስል Reuters

Ber. USA (Neuer USA_ Botschafter für Äthiopien) - MP3-Stereo

የአሜሪካ የዉጭ ሚኒስትር ጉዳይ መስርያ ቤት ሹመታቸዉን አስመልክቶ ከዶይቼ ቬለ ለቀረበላቸዉ ጥያቄ ከአፍሪቃ ሃጋሮቻችን ጋር በአፍሪቃ ነፃ ፍህታዊና ተዓማኒነት ያለዉ ምርጫን ለማካሄድ ድጋፍ እናደርጋለን የአፍሪቃ አቅዋም በዚህ በኩል ከአጋሮቻችን ጋር ቀጣይነት ይኖረዋል የሚል መልስን ነዉ የሰጡት። አንድ የምስራቅ አፍሪቃ የፖለቲካ ተንታኝ አምባሳደሩ ዲፕሎማስያዊ ብቃታቸዉ እንደ ዋና መስፈርት ታይቶ መታጨታቸዉን ገልፀዋል። የዋሽንግተኑ ወኪላችን መክብብ ሸዋ ዝርዝሩን ልኮልናል።     

መክብብ ሸዋ


አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ