1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኤኮኖሚ

ለአፍሪቃ የፖሊሲ አማራጮች የሚጠቁመው መፅሐፍ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 9 2010

አፍሪቃ አሁን ካሉባት ችግሮች እና ወደ ፊትም ከሚያጋጥሟት ፈተናዎች ልትወጣ የምትችልባቸውን ሥልቶች የሚጠቁም እና የፖሊሲ አማራጮችን የሚያሳይ ነው የተባለ መፅሐፍ ባለፈው ሳምንት በብራስልስ ተመርቋል።

https://p.dw.com/p/2mBzk
Symbolbild Libyen Algerien Ägypten Maghreb Nordafrika
ምስል Fotolia/Elenathewise

አማራጭ ፖሊሲ ለአፍሪቃ

317 ገፆች ያሉት መፅሐፍ Making Africa Work የተሰኘ ርዕስ አለው። ጸሐፊዎቹ ለበርካታ የአፍሪቃ ፕሬዝዳንቶች በአማካሪነት ያገለገሉት ግሬግ ሚልስ፤ በአፍሪቃ ላይ ያተኮሩ መፃህፍት ከዚህ በፊት ለንባብ ያበቁት ጄፍሪ ሔርብስት፣የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ እና የቀድሞብ የብሪታኒያ ጦር ባልደረባ ዲኪ ዴቪስ ናቸው። ፀሀፊዎቹ ያነሷቸው ሐሳቦች እና የጠቆሟቸው የመፍትሔ አስተያየቶች ወቅታዊ የመሆናቸውን ያህል የአፍሪቃ ፖሊሲ አውጪዎች እና አስፈፃሚዎች ይጠቀሙባቸዋል የሚል ተስፋ ተሰንቋል። 
ገበያው ንጉሴ
እሸቴ በቀለ
ኂሩት መለሰ