ለአፍሪቃ ዕድገት የሳይንስና ቴክኖሎጂ አጋርነት፣
ረቡዕ፣ ሚያዝያ 12 2003ማስታወቂያ
የአፍሪቃ ኅብረት አባል ሀገራት ከ 3 ዓመት በፊት፤ ካልተጣራ ብሔራዊ ገቢያቸው ፣ ቢያንስ 1 ከመቶውን ለሳይንስና ሥነ-ቴክኒክ ለማዋል ተስማምተው እንደነበረ ቢታወስም፣ ተግባራዊነቱ፤ እንደስምምነቱ አለመሆኑ ነው የሚነገረው። መንስዔው ምን ይሆን? የሥነ-ቴክኒክ ዝውውር የሚሰኘውስ፣ ጠቀሜታው እስከምን ድረስ ነው? የአፍሪቃ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፤ የፈጠራና ልማት ፣ የኢንተርኔት ዓምደ- መረብ ሚና እንዴት ይታያል? የዛሬው ሳይንስና ኅብረተሰብ ዝግጅት፣ ለአፍሪቃ ዕድገት የሳይንስና ቴክኖሎጂ አጋርነት በሚል ርእስ አንድ የዘርፉን ባለሙያ ለቃለ-ምልልስ ጋብዟል።
ተክሌ የኋላ
ሸዋዬ ለገሰ