ለአዲስ አበባ ንጹህ የመጠጥ ውሐ አቅርቦት ማሻሻያ
ዓርብ፣ ሰኔ 12 2007ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የአየር ንብረት ጥናት ማዕከል ወጣት ተመራማሪዎችንና በዘርፉ የተሰማሩ ባለሃብቶችን ያሳተፈ ዐውደ ጥናት አዲስ አበባ ውስጥ አካሄደ ። ዐውደ ጥናቱ በተለይ የኢዲስ አበባን ንጹህ የመጠጥ ውሐ አቅርቦት ማሻሻል በሚቻልበት መንገድ ላይ ያተኮረ ነበር ። በዓውደ ጥናቱ ላይ የከተማይቱ ነዋሪ ሊያገኝ ይችል ከነበረው ውሐ ከፊሉ ብቻ እንደሚደርሰው ተገለጿል ። ለዚህም በምክንያትነት ከተጠቀሱት ውስጥ ደለልና ውሃው ተጠቃሚው ጋ ሳይደርስ መፍሰሱ ናቸው ። በዐውደ ጥናቱ ላይ ለችግሩ መፍትሄ ይዘው የቀረቡት ወጣት ተመራማሪዎች ሃሳባቸውን አካፍለዋል ።የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝር አገባ አለው ።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ