ለትንበያ ያስቸገረው የብሪታኒያ ምርጫ
ረቡዕ፣ ሚያዝያ 28 2007ማስታወቂያ
ነገ በመላ ብሪታኒያ በሚካሄደው አጠቃላይ ምርጫ የሚሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዛሬ የመጨረሻ የምርጫ ዘመቻቸውን አካሂደዋል ።ባለፉት 5 ሳምንታት በተካሄዱት የምርጫ ዘመቻዎች ከዋነኛዎቹ ተፎካካሪዎች ከወግ አጥባቂው ፓርቲ እጩ ዴቪድ ኬምረንም ሆነ ከሌበር ፓርቲው ተወዳዳሪ ኤድ ሚሊባንድ ማንኛቸው የመሪነቱን ቦታ ሊይዙ እንደሚችል ግልፅ አልነበረም ። በዚህ የተነሳም የነገው አጠቃላይ ምርጫ ውጤት ምን ሊሆን እንደሚችል ለመገመት አስቸጋሪ ሆኗል ። በአሁኑ ምርጫ እስከዛሬ ብዙም ድጋፍ ያልነበራቸው ፓርቲዎች የተሻለ ድምጽ ሊያገኙ ይችላሉ ተብሎ ይጠበቃል ።ስለ ነገው የብሪታኒያ አጠቃላይ ምርጫ የለንደኑን ዘጋቢያችንን ድል ነሳ ጌታነህን ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሬዋለሁ ።
ድል ነሳ ጌታነህ
ኂሩት መለሰ
ተክሌ የኋላ