1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለቆዳ ሊደረግ የሚገባዉ ጥንቃቄ

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 10 2010

ሰዎችን ወደ ህክምና እንዲሄዱ ከሚያደርጓቸዉ አስር የህመም አይነቶች የቆዳ የጤና ችግር አንዱ ነዉ። የፀሐይ ብርሃንም ሆነ ሙቀት ለሰዉነታችን ቆዳ የሚያስፈልገዉን ያህል ከመጠን ሲያልፍ ደግሞ ችግር እንደሚያስከትልበት የዘርፉ የህክምና ባለሙያዎች ያመለክታሉ።

https://p.dw.com/p/2pf54
Frau Gesicht Peeling Symbolbild
ምስል Colourbox/Serghei Starus

ቆዳ ላይ የሚታየዉ የዉስጥ ወይም የዉጫዊ ችግር መገለጫ ነዉ፤

 ቆዳችን የሰዉነታችን የዉስጥ ክፍሎች መከለያ እንደመሆኑ ለተለያዩ ጉዳቶች የተጋለጠ ነዉና ተገቢዉ ጥንቃቄ እንዲደረግለትም ይመክራሉ። ቆዳ ላይ የሚወጡ ማናቸዉም ነገሮች በዉስጥ ካለ ሌላ ህመም ወይም በዉጭ በተለያየ ምክንያት ቆዳ ላይ ከሚደርሱ አደጋዎችም ሆነ ጉዳቶች ጋር ሊገናኝ ስለሚችል የዘርፉ ሃኪሞች ጊዜ ወስደዉ ተገቢዉን ምርመራ በማድረግ ሊለዩት ይገባል። በብርድ ጊዜ እሳት መሞቅን ጨምሮ ኬሚካሎችንም ሆነ ለሰዉነታችን ባዕድ የሆኑ ነገሮችን ሊያስከትሉት የሚችሉት ስለማይታወቅም ጥንቃቄ ማድረጉ አስፈላጊ ነዉ። በተለያየ ምክንያት የሚወሰዱ መድኃኒቶች እንዲሁም አመጋገባችንም የቆዳችንን ጤንነት ለማወክ የራሱን አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያበረክት ይችላል። በአዲስ አበባዉ አለርት ሆስፒታል ልዩ ሃኪሙ ዶክተር ሽመልስ ንጉሤ ቆዳን ለችግር የሚዳርጉ መንስኤዎችን እና ባጠቃላይም ለዉበት ሲባል የሚቀቡ ቅባቶችን አስመልክቶ አስቀድሞ መደረግ ይገባል ያሉትን ሙያዊ ምክራቸዉንም ለግሰዋል። ሙሉ ቅንብሩን ከድምፅ ዘገባዉ ያድምጡ፤

ሸዋዬ ለገሠ

እሸቴ በቀለ