ለስደተኞች የሚውል የጀርመን ርዳታ ለኢትዮጵያ
ሐሙስ፣ ነሐሴ 22 2006የጀርመን መንግሥት ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ ስደተኞች የምግብ ርዳታ አቅርቦት የሚውል 750,000 ዩሮ ርዳታ ሰጠ። በአፍሪቃ ስደተኞችን በማስተናገድ ረገድ በወቅቱ የአንደኛነቱን ደረጃ የያዘችው ኢትዮጵያ ገንዘቡን ለሚቀጥሉት አራት ወራት ለስደተኞቹ የሚያስፈልገውን ምግብ ለማቅረቢያ እንደምታውለው የጀርመን ኤምባሲ አስታውቋል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
አርያም ተክሌ