1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለማርስ ጉዞ የሚደረገው ቅድመ-ዝግጅት፣

ረቡዕ፣ ግንቦት 25 2002

ዓለም ፣ ባሁኑ ወቅት፣ በፖለቲካ ፣ በኤኮኖሚና ማኅበራዊ ኑሮ ችግሮች በተለይም በፋይናንስ ቀውስ ተወጥራ እንደምትገኝ እሙን ነው።

https://p.dw.com/p/Ng1Z
ማርስምስል picture-alliance/ dpa

ከማጡ ለመውጣትና በኤኮኖሚ ለማንሠራራትም ሆነ ብልጽግና ለማግኘት፤ ሳይንስ አብነቱን በማፈላለግ ረገድ ፣ሰፊ እርዳታ ሊያበረክት እንደሚችል የሚያጠራጥር አይደለም። ሳይንስና ሥነ ቴክኒክ ዘርፈ-ብዙ እንደመሆኑ መጠን፣ ጠበብት፣ የቅርቡን ትተው በሩቁ የአሠሣም ሆነ የምርምር ትልም ላይ ስለማትኮራቸው በየጊዜው የምንሰማውና የምናየው ጉዳይ ሆኗል። ለማወቅ ጉጉት ያለውን አእምሮ ለማርካት ካልሆነ በስተቀር፣ እስካሁን ሰፊ ምርምር ለሚያደርጉት አገሮች ህዝብም ሆነ በአጠቃላይ ለዓለም ህዝብ፣ ከቋቱ ጠብ ሳይልለት ሰፊ ወጪ ከሚያስወጡት ሳይንሳዊ ተልእኮዎች መካከል አንዱ፣ ሌሎች ዓለማትን ለማሰስ አቅድ የተነደፈለት የኅዋ ጉዞ ነው። የኅዋው ጉዞ፣ አስቀድሞ በምድር ላይ ሰፊ ዝግጅትን የሚጠይቅ እንደመሆኑ መጠን፣ ለምሳሌ ያህል፤ ሰው ወደማርስ ለመላክ ብዙ ጊዜ ሲነገርለት የቆየውን የረጅም ጊዜ እቅድ፣ ትንሽ ቀረብ ለማድረግ በነገው ዕለት ሞስኮ ውስጥ፣ ክብረ-ወሰን የሚይዝ፣ የ 520 ቀናት ልዩ ዝግጅት ይጀመራል።

ወደ ማርስ ለመጓዝ፣ አስቀድሞ ልምምድ የሚደረግበት ዝግጅት ለ2 ኛ ጊዜ፣ ነገ ሲጀመር ፤ 6 ሰዎች የዚህ ተልእኮ አስፈጻሚዎች ይሆናሉ። የተመረጡት 6 ሰዎች፣ 520 ቀናት ከውጭው ዓለም ጋር ሳይገናኙ፣ ጊዜያቸውን በጠባብ ቦታ፣ ቤተ-ሙከራ( ላቦራቶሪ )በመሠለ ሥፍራ፣ ይሆናል የሚያሳልፉት። የዚህ ፣ ብርቱ ዲሲፕሊንም ሆነ መሥዋእትነት ጠያቂ መርኀ-ግብር ተሳታፊዎች፤ 3 ሩሲያውያን፣ አንድ የፈረንሳይና አንድ የኢጣልያ ተወላጅ እንዲሁም አንድ ቻይናዊ ናቸው።

ተክሌ የኋላ