ለሕዝብ አገልግሎት ሰጪ የመንግሥት ተቋማትና ተግዳሮቶቹ
እሑድ፣ ሰኔ 29 2006ይህ በተለይ ከመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማትም ሆኑ መሥሪያ ቤቶች በእጅጉ የሚጠበቅ ነው። ከሥርዓቶች ለውጥ ጋር የመንግሥት መ/ቤቶችን አያያዝም ሆነ አመራር የታዘቡ አንዳንድ ተመራማሪዎች እንደሚሉት ከሆነ፤ የብቃት ማነስ ብቻ ሳይሆን ብልሹ አሠራርም ፣ ዕድገት ፈላጊዎች አጥብቀው የሚሹትን ውጤት ማስገኘት አልቻለም። የተባበሩት መንግሥታት የህዝብ አገልግሎት አሰጣጥ መታሰቢያ ዕለት ዘንድሮ ሰኔ 16 ቀን 2006 ነው ታስቦ የዋለው።የታዳጊው ዓለም ባልደረባ በሆነችው ኢትዮጵያ ደግሞ ፣ ዘንድሮ በተጨማሪ ለ 2 ሳምንታት እስከ ሰኔ 30 እንዲታሰብ በመደረጉ እስከዛሬም ሆነ ነገ ይዘልቃል ማለት ነው።
ለሕዝብ አገልግሎት ሰጪ የመንግሥት ተቋማትና ተግዳሮቶቹ፣ የዛሬው የውይይታችን ርእስ ነው ፣ ለዚህም እንግዶች ጋብዘናል፣ ከመንግሥት የሲቭል አገልግሎት ሰጪ ሚንስቴር በኩል ተሳታፊ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም ፤ ሐሳባቸውን ግን በአጭሩ አካተናል ። ለዛሬው ውይይት ቀጠሮ አክብረው የተገኙልን 3 ተሳታፊዎች ፤ የተለያየ ሙያ ይኑራቸው እንጂ እንደማንኛውም ዜጋ የተጠቀሰው መ/ቤት ተገልጋዮች ናቸው። ወ/ሮ ራሔል አየለ ፣ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ኮንፈደሬሽን የሴቶች ጉዳይ መምሪያ ኀላፊ ፣ ዓለማየሁ አበበ፣ የባለራእይ ወጣቶች ማሕበር ሊቀመንበር ፣ እንዲሁም የአዲስ አበባው ዘጋቢአችን ጋዜጠኛ ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ናቸው።
ተክሌ የኋላ
አዜብ ታደሰ