ለሌላ ሀገር የሚሮጡ አትሌቶች
ዓርብ፣ ነሐሴ 10 2005ማስታወቂያ
በተለይም በሞስኮ በመካሄድ ላይ በሚገኘዉ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዜግነታቸዉን የቀየሩና በሌሎች ሀገራት ሰንደቅ ዓላማ ስር የሚወዳደሩ ኢትዮጵያዉያን አትሌቶች ቁጥር ከመቼዉም ጊዜ ይበልጥ ከፍተኛዉን ቁጥር መያዙን ትገልጻለች በስፍራዉ የምትገኘዉ ዘጋቢያችን ሃይማኖት ጥሩነህ። እናም ትላለች ሃይማኖት ለአትሌቶቹ ፍልሰት በርካታ ምክንያት ቢጠቀስም ጉዳዩ ግን አሳሳቢ መሆኑን ብዙዎች ይስማሙበታል። በሌላ በኩልም በርካታ ተፎካካሪ አትሌቶች ላሉዋት ሀገር በታላላቅ ዉድድር ለመካፈል ሌሎች አማራጮችን መጠቀም አለባቸዉ የሚሉ ወገኖችም መኖራቸዉን ትገልጻለች። ለዝርዝሩ ሃይማኖት
ሃይማኖት ጥሩነህ
ሸዋዬ ለገሠ
ሂሩት መለሰ