1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ህፃናትና ቋንቋ በባዕድ ሀገር

እሑድ፣ የካቲት 15 2001

ከህጻናቱ መካከል የተወሰኑት ጥያቄዬ ግራ ገብቷቸው ይመለከቱኛል። በዕድሜ ከሌሎቹ ትንሽ ከፍ የምትለዋ የሰባት ዓመቷ ህፃን ሳቢፋት በጀርመንኛ ጠየቀች።

https://p.dw.com/p/GvOn
ህፃናትና ቋንቋ
ህፃናትና ቋንቋምስል UNO
ቓንቓ አንድ ማህበረሰብ ማንነቱን፣ እሴቱንና ባህሉን የሚጠብቅበት ቁልፍ መሳሪያው ነው። ቓንቓ ከምንም በላይ ደግሞ እርስ በርስ ለመግባባት ወሳኝ ነገር መሆኑ ለማንም ግልፅ ነው። በውጭው ዓለም የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ከእለት እለት ቁጥሩ እየተበራከተ ከመሄዱ የተነሳ ስፍር ቁጥር የለውም ማለት ይቻላል። ታዲያ ለመሆኑ ለዘመናት ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ እኛ ዘንድ የደረሰውን ቓንቓችንን፤ ሀገራቸውን በቅጡ ለማያውቁና በባዕድ ሀገራት ለተወለዱ ልጆቻችን የምናቀብልን ስንቶቻችን እንሆን? ለዛሬ እዚህ ጀርመን ሀገር የአንድ ህጻን ኢትዮጵያዊ በዓል ላይ የተሰባሰቡ ህጻናትና ወላጆቻቸውን እናገኛለን።