ሃዉሳ ቋንቋ
ሰኞ፣ ነሐሴ 28 1999ማስታወቂያ
ከእነዚህ ቋንቋዎች መካከል ኪስዋሂሊ፣ አማርኛ እና የሃዉሳ ቋንቋዋ በአፍሪቃችን በሰፊዉ ይነገራል። የዶቸ ቬለ ራድዮ ጣብያ በሃዉሳ ቋንቋ በየቀኑ ለመካከለኛዉ እና ለምዕራብ አፍሪቃ ስርጭቱን ያሰማል። ሰሞኑን የዶቸ-ቬለ ራድዮ የሃዉሳ ቋንቋ ዝግጅት ክፍል ለአድማጮቹ፣ በሃዉሳ ቋንቋ ዉስጥ ተወዳጅ ቃል የቱ ነዉ ሲል የመዘርዝር ጥያቄ አቅርቦ፣ በርካቶች ይህ በሃዉሳ ቋንቋ ተወዳጅ ነዉ፣ ሲሉ መልሳቸዉን አሰምተዋል። ተወዳጅ ቃል በሃዉሳ ምን ይሆን የስርጭት ክፍሉን ሃላፊ አነጋግረናል። በተጨማሪ ስለ በሃዉሳ ቋንቋ ተናጋሪዎች ዘንድ ያለ የሰርግ ባህል ልናወራችሁ ተዘጋጅተናል