1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት ድል 71ኛ ዓመት

ሰኞ፣ ግንቦት 1 2008

ያለፈዉን ድል ከመዘከር ይልቅ የሩሲያን ወታደራዊ ጡንቻ ለማሳየት ያለመ የመሠለዉን ወታደራዊ ሠልፍና ትርዒት ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲንና ከፍተኛ ባለሥልጣኖቻቸዉ ተከታትለዉታል።

https://p.dw.com/p/1Ikhj
ምስል Reuters/S. Karpukhin

የሶቭየት ሕብረት ጦር የናትሴ ጀርመን ጠላቱን ድል ያደረገበት 71ኛ ዓመት በዓል ዛሬ ሞስኮ ዉስጥ በደማቅ ወታደራዊ ሥርዓት ተከብሮ ዋለ።የያኔዉ ቀዩ ጦር የሩሲያን ገሚስ ግዛት ተቆጣጥሮ የነበረዉን የናትሴ ጀርመን ጦርን ከሶቬት ሕብረት ግዛት አልፎ ከመላዉ ምሥራቅ አዉሮጳ ጠራርጎ አስወጥቶ ከፊል በርሊንን ለመቆጣጠር ከተባባሪዎቹ ሐገራት ጦር ሁሉ የመጀመሪያዉ ነበር።ሰባ አንደኛዉ ዓመት ዛሬ ቀዩ አደባባይ-ሞስኮ ዉስጥ ሲከበር ከ10 ሺሕ የሚበልጡ እግረኛ ወታደሮች፤ ዘመናይ ታንኮች፤ ኑኩሌር ማወንጨፍ የሚችሉ ሚሳዬሎች ሲሰለፉ፤ SU 35 የተሰኘዉን ዘመናይ ተዋጊ ጄትን ጨምሮ የተለያዩ ተዋጊ አዉሮፕላኖች በዓየር ልዩ ትርኢት አሳይተዋል። ያለፈዉን ድል ከመዘከር ይልቅ የሩሲያን ወታደራዊ ጡንቻ ለማሳየት ያለመ የመሠለዉን ወታደራዊ ሠልፍና ትርዒት ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲንና ከፍተኛ ባለሥልጣኖቻቸዉ ተከታትለዉታል።ፑቲን በዚሁ ሥርዓት ላይ ባሰሙት ንግግር አሸባሪነትን ለመዋጋት መንግሥታት በጋራ እንዲቆሙ ጠይቀዋል።በሁለተኛዉ ያዓለም ጦርነት ወቅት ሶቬት ሕብረት 27 ሚሊዮን ወታደርና ሠላማዊ ሰዉ አልቆባታል።